ልጥፎችን በመለያ Amharic Poem በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ
ልጥፎችን በመለያ Amharic Poem በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ

ማክሰኞ 26 ጁን 2018

አገሬ አለኝ ሰው ሰው

   
      ሰው ሰው አለኝ ሃገሬ፣
     በፍቅር አጥር ታጥሬ፣
     እሙ ለአብዩ የፍቅር ገበሬ፣
     ምርጥ ዘር የዘራሽ ትላንት በሃገሬ፣
    ይኸው አበላሽን የፍቅርን ፍሬ፡፡

ህዝቡ ባንድ ተሞ ተሰብስቦ ሳየው፣
ጠረኑ አለኝ ሰው ሰው፤
አገር ማለት ሰው ነው፣
ሰው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡

        መሪ እጅ ሲነሳኝ፣
       የሰው ክብር ሲሰጠኝ፣
       አገር ማለት ሰው ነው፣
      የሚለውን ዘፈን ልቤ እየመለሰው፣
      አገሬ አለኝ ሰው ሰው፡፡

ፍቅር የሚገደው፣
ሲያመኝ ሚጨንቀው፣
ስሞት የሚያለቅሰው፣
ወገኔን ስላየሁ፣
አገሬ አለኝ ሰው ሰው፣
ፍቅር የሚገዛው፣
ፈጣሪ ተመስገን ይህን ቀን ስላየሁ፡፡


     

ማክሰኞ 3 ጃንዋሪ 2017

Rabi'a poem 2

Translation in Amharic by Tirsit Endeshaw

የወደድኩህ እንደው ሲኦልን ፍራቻ፣
በሳቱ አንድደኝ እንዲያው እኔን ብቻ፤

            ገነትን ፈልጌም ካልኩህ አምላኬ ሆይ፣
            ከመንግሥትህ ደስታ በፍፁም እኔን ለይ፤

ዓይኔ አንተን አንተን ሲያይ ለፍቅርህ ስርቅታ
እባክህ አትጋርደኝ ከመለኮት ደስታ፡፡

ቅዳሜ 24 ዲሴምበር 2016

Rabi'a poem

Translation in Amharic by Tirsit Endeshaw


ባንድ እጄ ውሃ ይዤ ባንዱ ነበልባል፣
ሲኦልን ላጥፋና ገነትን ላቃጥል፤

ፀሎቴ እንዳይበዛ ለገነት ጓጉቼ
አምላኬን እንዳልወድ ሲኦልን ፈርቼ፤

የነሱ ሁኔታ አይሆንህም እቻ፡፡
ፍቅርህን እንዳስብ ላንተነትህ ብቻ፡፡

ማክሰኞ 20 ዲሴምበር 2016

አዳም ከኛ እንዳንዱ ሆነ

በሥጋው ተራክቦ ሰው እየፈጠረ፣
እስትንፋስም ጠቅሶ በህይወት አኖረ፡፡
ተመቻቸለት ምቾቱን ጨመረ፣
ለተጣሉት እንዲሁ በሳት አባረረ፣
እልህም ተጋብቶ ጥል እያከረረ፡፡

     መንገድ የራቀው ለት ሲሰራ መኪና፣
     ጐረበጠኝ ብሎ አስፋልቱን አቀና፣
     ለጥቆም መርከቡን ውሃውን ለመክፈል፣
     እንደው ምኑ ቀረው ሲፈጥር ሲፈጥር ...

ኃይል አጠረኝ ብሎ ከሰል አነደደ፣
ኃይል አነሰኝ ብሎ ውሃውን ዘወረ፣
በኃይልም አይሎ ምርቱንም ጨመረ፣
አሁንም ኃይል አንሶት ኒውክለር አብላላ፣
አዳምዬ ሞኙ እጅጉን ተላላ፣
ኃያልነት ለምዶ ልቡ ትዕቢት ሞላ፡፡

     በነካ እጁ ደግሞ ፍቅርንም ተማረ፣
     የበደሉትንም በነፃ እየማረ፡፡
     ለራባቸው ምግብ ልብስም ለታረዙት፣
     ለመርዳት ሲታትር ነቅቶ በኃላፊነት፡፡

ብልህ የሆነውን ቴክኖሎጂ ፈጥሮ፣
እያደር ምቾቱን አብዝቶ ጨምሮ፣
ልቡን ሰጠው ደግሞ ምጡቁን አዕምሮ፣
የበለጠው መስሎት ከራሱ ተፈጥሮ፡፡

      ከኛ እንዳንዱ ሆነ ፈጠራን ጨመረ፣
      የራሱ ሰው ሽቶ ሮቦትም ፈጠረ፣
      እሱም ተሻሽሎ በየለት ዳበረ፣ 
      በስሜት በውበትን እየተበጠረ፡፡

ከኛ እንዳንዱ ሆነ የሥላሴ ስላቅ፣
በስልጣን ላይ ስልጣን በየቀኑ ሊረቅ፣
ቃል ኪዳን ሆነልን በየቀኑ የሚልቅ
እንዳመነው መጠን ስንንኖር የሚመረቅ፡፡
     

ዓርብ 9 ዲሴምበር 2016

መሻቴ

መሻቴ እኔን ሽቶ፣
ፍለጋውን ለፍቶ፣
ካለሁበት መጥቶ፡፡

መኖርን ሻትኩና፣
እሱም ተገኘና፣
ፈታ ተባለና፣
ዳግም ተሰልችቶ፣
ሌላ መሻት መጥቶ፣
ደግሞ እሱም ወጥቶ፣
መጥቶ ወጥቶ፣
መጥቶ ወጥቶ …..

ዳግም ልቆ መጥቶ፣
ተገኝቶና ወጥቶ፣
እምነትን ተራራ ልቤ ላይ ገንብቶ፣
ላይመለስ ሄደ ቤቴን ተሰናብቶ፡፡

ሐሙስ 29 ሴፕቴምበር 2016

የበሬው ስጋት

ማክሰኞ 6 ሴፕቴምበር 2016

አሸንዳ

አሸንዳ
የኔ ልጅ አበባ የኔ ነጭ ወረቀት፣
በቴሌቪዥን መስኮት አይታ እንደገባት፣
ቀጤማ አገልድማ የምትጨፍርበት፣
ለአሸንዳ በዓል ባመት አደረሳት፡፡
እኔም በዚሁ መስኮት መረጃ የሰማሁት፣
የከተማው ቧንቧ ውሃ መስጠት ማቃት፣
ያሸንዳን ሌላ ገጽ ስኖር አሳየኋት፡፡
ይሄንን አሸንዳ ቅርስ ነው ያላችሁ፣
የኔን ቤት አሸንዳም አትርሱት ባካችሁ፡፡



ረቡዕ 27 ኤፕሪል 2016

ክርክም

ክርክም እንደ አትክልት፣
ክርክም እንደ አፍሮ፣
በስግደት መከርከም፣
በጽሞና ማረም፣
በፆም ለመገረዝ፣
ይበቃል መደንዘዝ፣
በኑሮ ላይ መፍዘዝ፡፡

ደግሞም እንበል ቀና፣
ጨመር አርገንበት ፍቅርና ትህትና፣
ልዩነት መኖሩ ይሞላላልና፡፡

ክርክም .. ክርክም … ክርክም ፣
የልቦናን ክፋት በፅሞና እክም፣
የትዕቢትን ነገር በፆም በማዳከም፣
የጉልበትን ግነት በስግደት ማለዘብ፣
ሰዋዊ ድግመትን በፆም መቀስ ክርክም፡፡

ዓርብ 24 ጁላይ 2015

ሞት እንደሌለ አየሁ

አባቴ ሁልጊዜ ኑርልኝ ከጐኔ፣
በክፍ በደጉ እንድትሆነኝ ወኔ፣
ስመረቅ ትምህርቴን እንድትኮራብኝ፣
ስዳር ስሞሸርም እንድትቆምልኝ፡፡

ልጆቼም ይምጡና ይቦርቁ ፊትህ፣
ልፊያቸውም ቻል እስኪዝል ጉልበትህ፣

ልጆቼንም ይዤ መርቀኝ ልምጣና፣
ሳስመርቅ ስድርም ባለም እቤቴ ና፡፡

መቼ ይጠገባል የወላጅ መኖሩ፣
ያሳቅቃል እንጂ የሞት ዙር ማክረሩ፡፡

ልጆቼ ጠየቁ መቼ ይመጣል አሉ፣
ሞተ’ እንዳልላቸው ጠጠረብኝ ቃሉ፤

በቃሉ ተምሬ ከሞት ወዲያ ህይወት፣
ተቀብዬው ኖሬ በልበ-ሙሉነት፣
ዛሬ ባንተ መሞት እምነቴ ሆነ እውነት፤

ከሞትክም በኋላ እንዳለህ ስላየሁ፣
አባቴ ባንተ ሞት - ሞት እንደሌለ አየሁ፡፡

ከሞትክም በኋላ እንዳለህ ስላየሁ፣
አባቴ ባንተ ሞት - ሞት እንደሌለ አየሁ፡፡

አባቴ በሞትህ ዛሬም ተምሬአለሁ፣
ፍቅርህን ሞተህም ዛሬም አየዋለሁ፣
የፍቅር መምህሬ እኔም ‘ወድሃለሁ፡፡

ሰኞ 25 ሜይ 2015

ሂውማን ሄር

በህንድ ሃገር የተራበች፣
ፀጉሯን ሸጣ እየበላች፣
ኑሮን ለዕለት እየገፋች፣
ነገም ሲያድግ እየላጨች፣
የአለሙን ሴት ታስውባለች፡፡

ሂውማን ሄር  - የሰው ፀጉር፣
በብር መጥቶ የሚያምር፣
ላለው ማማር የሚገበር፡፡

የራስ አፍሮ አሳፍሮ፣
ከሰው በታች ሆኖ አሮ፡፡

የራስ ፀጉር ለማሳደግ፣
ጊዜ ይፈጃል አይልም ብድግ፣
ገንዘብ ካለ ሊንዠረገግ፣
የሰው ፀጉር ባለማዕረግ፡፡

የድሃዋ ምሣ መብያ፣
የኔ በየለት መዋቢያ፣
ባናቴ ላይ ተቆልሎ፣
እኔነቴንም ከልሎ፣
እንዳያስረሳኝ ጠቅልሎ፡፡

ማክሰኞ 27 ጃንዋሪ 2015

ለኛ ነው ጨለማ?

ግብር ከፍለን ከፍለን፣
ጊቢን 3 ገድበን፣
አባይንም ደግመን፣
ቦንድ ሁለቴ ገዝተን፣
በየቀኑ A ባልን፣
ገቢዎች በሰማ፣
ለኛ ነው ጨለማ?


ረቡዕ 5 ኖቬምበር 2014

ዝም አሰኘኝ

ፍቅሩንም ለመቅመስ፣
ቃሉን ለማወደስ፣
ለመስማት ሲቀደስ፣
ከፍላጐት ንፋስ፣
አደረገኝ ትንፍስ፡፡

ሃሳቤን ሞላልኝ፣
ሁሉ ተሳካልኝ
ፀሎት አለቀብኝ፣
በፈቃዴ አዋለኝ፡፡
በደስታ ቦርቃ
በምስጋናው ልቃ፣
ልቤን ደስ እያለኝ፣
ብቻ ዝም አሰኘኝ፡፡

ሰኞ 24 ፌብሩዋሪ 2014

ውሃን ለፍቅር

የአባይ ተፋሰስ ውሃ ተጣጪዎች፣
ባንድ የተጋበዙ የግዜር ታዳሚዎች፣
ውሃ ከሰማይ ላይ መሆኑን ተረድተን፣
ትብብር ላይ ሆነን አብረን እየሰራን
ተስማምተን ልንጠጣ ባንድ ከተሰጠን፣
በቅናት ነደደ ፍቅር ጠላ ሰይጣን፡፡

ስስትን ዘራና በግብጽ ጋዜጦች፣
ቁጣን ጨመረና በግብፅ የሰው ልቦች፣
መገፋፋት መጣ ወደኃላ ማለት፣
ጠልተውንም ሳይሆን ብቻ ለራስ ማድላት፡፡

የጥል መሠረቱ ነውና ዲያቢሎስ፣
የልቡ አምሮቱ እንድንጨራረስ፡፡
ስልጣኑም ተሰጥቶት ሊፈትን ከጌታ፣
ያናፍስብናል የስስት ጫጫታ፡፡

ቸግሮት አይደለም የሰጠን ባንድ ላይ
እንድንኖር ሽቶ ነው እንዲህ ሳንለያይ፣
ከሰይጣን እንድንበልጥ በደንብ እናውቃለን፣
ለትብብር ለፍቅር እንበረታለን፡፡

ረቡዕ 21 ኦገስት 2013

ቅዥቴን እንደህልም

በቁምህ ያለምከው አረንጓዴ ልማት፣
አገር ላገር ዞረህ ነጮቹን ለማድማት፣
አታክቶህ አታክቶህ የሆነብህ ቅዥት፣
ስራ ሁሉ ቀርቶ አደረግነው ዕውነት፡፡

እንደው ብታደለው ህዝብህን ለመምራት፣
ቀጥ ካለው አይኑ መሪውን በመፍራት፣
አንድ ቀን መርቼ ጆሮ ተሰጥቶኝ፣
ከዚያም በማግስቱ ሞት በወሰደኝ፤
ቅዥቴን እንደህልም እንዲፈቱልኝ፣
ሃገሬን ከሌቦች እንዲያተርፉልኝ፡፡

ዓርብ 2 ኦገስት 2013

ደጉና ጉረኛው

ደጉና ጉረኛው ተምታቱብኝና፣
ለመለየት ብዬ ጀመርኩኝ ብተና፡፡

እንኩ ብሉ ብሉ፣
ብትጠግቡም ጨምሩ፣
በላዩም ላይ ጠጡ፣
ማህበሬን አውጡ፣
በደንብ ተቀናጡ፡፡

አጃቢ እንዳያጣ፣
ለብቻው እንዳይወጣ፣
ለራሱ ጊዜ የለው፣

እንደው ሚበትነው፣
ለሚያካብበው፣
ደግነቱ ለሰው፣
ሰጥቶ እማይደመው፡፡

ዋጋውን ምስጋና፣
ተቀብሏልና፣
ሌላውን ሽቀላ፣
ተክቶታልና፣
ልዩነቱን እንጃ፡፡

ሌላው ደሞ ደጉ
ከሁሉ ሰው እኩል፣
ለመስጠት አይቸኩል፣
ቢሰጥ ለቸገረው
ቆርሶ ከሚጐርሰው
ደብቆ ከግራው፣
ምስጋና ሳያምረው፣
ለሰው የሚደንቀው፣
አይታይ ሲደማው፣
ሰው ሁሉ የሚያማው፡፡

ደጉና ጉረኛው፣
አንድነት አላቸው፣
ሁለቱም በጃቸው፣
መስጠት አለላቸው፣
የት ሄደ ዋጋቸው፣
ለየቅል ይምራቸው፡፡

ሰኞ 22 ጁላይ 2013

የተደበቀ እንቁ

ቅዳሜ የመሰሉ መዝለቂያየተረሳ ወራሽ የመጸሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ በዚህ በዓል ላይ ለእኔ እጅግ የደነቀኝ የደራሲዋ ንግግር ላይ ያየሁት አንድ ሴት ብቻ ያለፈችበት የማይመስል ጠንከር ያሉ የህይወት ተሞክሮዎች እና በዚህ ውስጥ ቀልጣ ሳትቀር ነጥራ የወጣች ሴት አየሁኝ፡፡  ይህች ሴት እራሱዋ ደራሲዋ መሰሉ መዘንጊያ ናት፡፡ በጊዜው ስለእርሱዋ የተሰማኝን ስሜት እንደዚህ ከተብኩት፡፡ መፍሐፉን ግን እናንተም ገዝታችሁ አንብቡት፡፡

መሰሉ መዝለቂያ ልጠይቅሽ አንዴ፣
የሚገኝ ከሆነ ለመስም ዘዴ፣
ልብሽን አውሺኝ ሲደክመኝ አንዳንዴ፡፡

በሳት ተፈትነሽ በደንብ ተበጥረሽ፣
ተረሳ ወራሽ አደባባይ ወጣሽ፣
ሆኜ እንደልጆችሽ በውነት ኮራሁብሽ፡፡

በሀገሬ በቅሎ ይህን መሰል ዕንቁ
አይ ኑሮ ክፋቱ ይህን መደበቁ፡፡

ተደበቀ እንቁ አግኝቻለሁ ዛሬ፣
እንግዲህ ልጠቀም በደንብ መንዝሬ፡፡

ማክሰኞ 9 ጁላይ 2013

ይሄም ይጋባል

በፍቅር ኑሮ ውስጥ ሲመጣ ፈተና፣
አንዱን ያሳምራል ሌላውን ሊያስቀና፣
አልያም የተወራ የሌላው ፈተና፣
ለሰማው በፊናው ጥያቄ ይፈጥርና፣
ነገሩን ያጋባል በንፋስ ጐዳና፡፡

ስንቱ ቤት ታምሷል በጐረቤት ፍቺ፣
ጥርጥር ተፈጥሯል በሌላው አምታቺ፣
ልብ ብለው ካላዩት የአይምሮን መንገድ
ልብ ውስጥ ሰርጐ ይገባል በባዶ መናደድ፡፡

ልቦች ተባበሩ ፍቅር ላይ አትክፉ፣
ፍቅርን ወላፈን አብሮ እንዳታጠፉ፡፡

የኑሮ ትክክል በሂሣብ ላይገኝ፣
ትዳራችን ላይ አንባባል እኝ-እኝ፡፡
ይልቅ የሰው ኑሮ ማየት ምን ያደርጋል፣
የነገር በሽታ በአይንም ይጋባል፡፡

ማክሰኞ 2 ጁላይ 2013

ወጣት ሆይ ውጣ

ወጣት ሆይ ውጣ ከእናትህ ቤት፣
በልጅነት አቅምህን ኑሮን ቅመሳት፣
ላብህ እንደሚያኖርህ በጊዜ ማየት፣
እንድታውቅ ይረዳል የኑሮን ብልሃት፡፡

ወጣት ሆይ ውጣ እናትህ ሳይደክማት፣
ብዙ ጊዜ የለህም ኑሮህን ለማድማት
መለስ ብለህ ደሞ እሷን ለመርዳት፡፡

በወላጆችህ ቤት ኑሮ እንኳ ቢሞላ፣
እንዳያዘናጋህ አትበል ወደኋላ፣
ፍቅር ይዟቸው እንጂ አይደሉም ተላላ፡፡

ያንተ ላብ እንዲበልጥ የጐበዙ ወጣት፣
ልብህ እንዲጠነክር ለኑሮ አቀበት፣
ዝቅ ካለው ኑሮ ሲነሱ አይተውት፣
የነገሩህ ታሪክ እነሱ የወጡት፣
ችላ እንዳትለው ይሁንህ እውቀት፡፡

ወጣት ሆይ ውጣ ኑሮን አሸንፈው፣
ዕድልን ተመልከት አይንህ ስር ነው ያለው፣
ጊዜህ የተሻለ የሰለጠነልህ
ክፉ የማታይበት ሰላም የሞላልህ፣
በተልካሻ ምክንያት አይዛባ ህልምህ፡፡

ወጣት ሆይ ውጣ ጉዋደኞችህን ለይ፣
እንዳትደናቀፍ ከመልካም ጉዞህ ላይ፣
እየጀመርክ ብቻ እንዳትሆን አባይ፣
መጽሀፍት ይኑሩህ በየቀን አለሁ ባይ፣
እንደብረት ጠንክር ለእሳትም ሁን ቀይ፣
ከፍታህን ጨምር በየቀን ወደላይ፣
ቀና ላሉ ሁሉ በቀላሉ አትታይ፡፡

ወጣት ሆይ ውጣ ድረስ ካለምክበት
ጊዜ እየገፋ እንዳይመስልህ ቅዥት
በርታ ጠንክርና አሁን ድረስበት፣
አዕምሮህን ይባርክ የሰማዩ አባት፡፡

ሐሙስ 20 ጁን 2013

እንደ ህፃናት?

እንደህፃናት ሁኑ እንደምቦቅቅላ፣
ልባችሁ ይታለል በእህል በሚበላ፣
ከነገርም ይልቅ ለጨዋታ ያድላ፡፡

እሪ ብለህ አልቅስ እንደው የከፋህ ለት፣
በውስጥህ አምቀህ አትሰጥ ለሀሜት፡፡

ነገ ምን ሊውጠኝ ብለህ አትጨነቅ፣
ዛሬን ብቻ ኑረው ልብህ እንዲቦርቅ
ወፎችን ያበላ ላንተም እንዲያውቅ እወቅ፡፡

ዓርብ 14 ጁን 2013

እንደዚህ ነው ፍቅር

ትላንትና እንደወትሮው ቀዝቃዛና ዝናባማ አየሩ ከሰዓት በኋላም ዘልቋል፡፡ ሆኖም እንደው ዣንጥላ ይዤ ከመውጣቴ የሚደንቅ ነገር በመስሪያ ቤታችን ግቢ ውስጥ ከሩቅ አየሁ፡፡ አንድ በሃያዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ ወጣት የሥራ ባልደረባችን አብረውት የሚሰሩ ባልደረቦቹ መስማት የሌለባቸው በጣም አስፈላጊ የስልክ ጥሪ ይመስለኛል ከቢሮ ውጪ የሚገኘው አረንጓዴ ሳር መሀል ላይ ሆኖ እጅግ ሞቅ ያለ ፈገግታና ሳቅ በተሞላ አነጋገር ይጫወታል፡፡ ዝናቡም ሆነ ብርዱ ትዝ ያለው አልመሰለኝም፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች አብሬው ፈገግ ብዬ ተመለከትኩት፡፡ በሱ ወንበር ተቀምጨ አልል ነገር አልተቀመጠም፣ በሱ ቦታ ቆሜ የሱን ስሜት ተሰምቶኝ ደስታውን ስላልቻልኩት በሰው ልጅ አዕምሮ ቋሚ የመረጃ ቋጥ (Hard disk) ውስጥ ሊቀመጥ የሚገባው ስሜት ሆኖ ስላገኘሁት ከዚህ እንደሚከተለው ከተብኩት፡፡

እንደዚህ ነው ፍቅር
ከሆነማ ላይቀር፣
እንደዚህ ነው ፍቅር፣
ከልብ የሚል ቅርቅር፣
ለትዝታ የሚቀር፡፡
የደወለች ለታ፣
ካሳየች ፈገግታ፣
ቀልጄም ከሳቀች፣
ብሎም ካደነቀች፣
አይን አይኔን እያየች
አለም ዘጠኝ ነች፣
ህይወቴ ደመቀች፣
ነፍሴ እየቦረቀች
ልታልፍ ተመኘች፡፡